ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ!

The House of People’s Representatives has adopted the new Criminal Procedure and Evidence Code as Proclamation No. 1410/2026

የ1954 የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት፣ በ1997 ከወጣው የወንጀል ሕግ፣ ሀገራችን ከምትተገብረው የወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ዛሬ የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን ከማስተዋወቁ በተጨማሪ የማስረጃ ሕግ በማካተት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የቆየውን አንድ ትልቅ ክፍተት ለመሙላት አስችሏል። ሕጉ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው።

የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በማርቀቅ ሂደት ከ15 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተለዩ ቁልፍ የሕግ ሪፎርሞች አንዱ ሆኖ፣ ብዙ ምክክር ተደርጎበት ሊጸድቅ ችሏል። ሕጉ ሀገር አቀፍ ተፈጻሚነት ያለው ሲሆን ከዚህ ሪፎርም የሚጠበቀውን ውጤት እውን ለማድረግ የፍትሕ ሚኒስቴር በሁሉም ደረጃ ከሚገኙ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል።

Relevant Departments and People
Tagged Under: act african charter on the rights and welfare of the child code criminal Criminal Procedure criminal procedure code decree ethiopian criminal procedure code Evidence house law legislation medicine and healthcare administration and control proclamation no. 661/2009 new no. Policy pro procedure proclamation proclamation no. Regulation representative Representatives res statute Use
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች