ከ14 ሺ ግራም በላይ የኮኬይን እፅ ይዞ የተገኘው ናይጄሪያዊ ዜጋ በፅኑ እስራት ተቀጣ

Nigerian Citizen Found in Possession of Over 14,000 Grams of Cocaine Sentenced to Rigorous Imprisonment

አሉይሲኡስ ኦኔን የተባለ የናይጄሪያ ዜግነት ያለው ተከሳሽ ልዩ ፈቃድ ሳይኖረው በሕግ የተከለከሉ እፆችን ከቦታ ቦታ ለማዘዋወር አስቦ ከብራዚል አገር ሳኦፖሎ ከተማ በመነሳት የኢትዮጵያን አየር መንገድ በመጠቀም ወደ ናይጄሪያ አገር ሌጎስ ከተማ ለመሄድ ህዳር 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ሲሆን ቦሌ አለም ዓቀፍ ኤርፖርት ለትራንዚት ባረፈበት ወቅት በተደረገበት ፍተሻ ሻንጣው ውስጥ ደብቆ 5 እሽግ ወይም 14‚319.69 ግራም የሚመዝን ኮኬይን አደገኛ እፅ ተገኝቶበታል፡፡

በመሆኑም ሰዎችን ሱስ በማስያዝ ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች መንስኤ እንዲሆኑ ስለሚገፋፋ እንዳይመረት፣ እንዳይዘዋወርና በጥቅም ላይ እንዳይውል የታገደውን ኮኬይን እፅ ፈቃድ ሳይኖረው ይዞ እየተጓዘ የተገኘ በመሆኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀኔራል ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወንጀል ሕግ አንቀጽ 525/1/ለ/ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ አደገኛ እፆችን ማዘዋወር ወንጀል ክስ መስርቶበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

ተከሳሹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ችሎት ቀርቦ የተከሰሰበት ክስ በችሎት ተነቦለት በወቅቱ ይዞት በነበረው ሻንጣ ውስጥ ምንም አይነት ኮኬይን ይዞ እንዳልነበር የገለፀ ሲሆን ዐቃቤ ሕግም በጉዳዩ ላይ የሚያስረዱ የሕግ ምስክሮችን አቅርቦ በማሰማት፣ ተከሳሹም በቀረበበት ክስ መሠረት እንዲከላከል ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ቢሰጠውም የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለት ባለማቅረቡ የመከላከል መብቱ ታልፎ በቀረበበት ክስ ስር በማስረጃ እንደ ክሱ አቀራረብ የተረጋገጠበት በመሆኑ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ20 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ሲል ወስኗበታል፡፡

Tagged Under: 1996 airport bole bole international airport Brazil cocaine conviction court Criminal Code drug drug smuggling Drug trafficking federal Federal High Court high imprisonment international international crime lideta narcotics nigeria paulo rigorous Rigorous Imprisonment sao sao paulo sentence trafficking Transnational crime
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች