የፍትሕ ሚኒስቴር እና የኢትየጵያ ማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ማህበር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነት ተፈራረሙ

Ministry of Justice and Ethiopian Community Radio Stations Association Signed a Cooperation Agreement

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ማህበር ለህብረተሰቡ የንቃተ ሕግ ማሳደጊያ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ሰምምነት ሰነድ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ በዋናነት የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን በመጠቀም የህብረተሰቡን የንቃተ ሕግ ግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ሲሆን የሁለቱ አካላትን የስራድርሻ በመወሰን የስራዉን አካሄድ ለመከታተል ያግዛል፡፡

የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ማህበር ከ70 በላይ ፈቃድ የተሰጣቸዉ ጣቢያዎች እንዳሉት እና ከነዚህም ዉስጥ 35 የሚሆኑ ሬዲዮ ጣቢያዎች ስርጭት ላይ ያሉ መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን፣ እነዚህ ሬዲዮ ጣቢያዎች ከ25 በላይ የአገር ዉስጥ ቋንቋዎችን በመጠቀም ስራዎቻቸው ተደራሽ እየሆኑ እንደሚገኝና በዚህም ህብረተሰቡ በቀላሉ በራሱ ቋንቋ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚያስችለዉ በስምምነቱ ወቅት ተገልፆል፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ ከተሰጡት ሃላፊነቶች አንዱ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መንገዶችን በመጠቀም የህብረተሰቡን ንቃተ ሕግ ማሳደግ አንዱ መሆኑን እና እስካሁን ባሉ ሂደቶችም በተለያዩ መንገዶች እየተሰራበት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህንን አጠናክሮ በማስቀጠል ረገድ እንዲሁም ተደራሽነታቸዉን ይበልጥ ለማጠናከር ያስችል ዘንድ የማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ስምምነቱን በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ኤርምያስ የማነብርሃን(ዶ/ር) እና በማህበሩ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎች ማህበር ሊቀመንበር አቶ እስማኤል ጡሀ እስማኤል አማካኝነት ተፈርሟል፡፡

Tagged Under: access access to information agreement Awareness broadcasting Capacity Building Civil Society community Cooperation cooperation agreement ermias yemaneberhan information legal Legal Awareness Legal Education memorandum Memorandum of Understanding partnership public radio radio broadcasting reform Stakeholder Engagement stations understanding
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች