ማስታወቂያ

Announcement

ለዐቃቤ ሕግ ደረጃ I እና ለዐቃቤ ሕግ ደረጃ II መደብ ላይ ለመቀጠር የጽሑፍ ፈተና ለወሰዳችሁ ተወዳዳሪዎች በሙሉ

ተቋማችን በዐቃቤ ሕግ ደረጃ I እና በዐቃቤ ሕግ ደረጃ II መደብ ላይ ዐቃብያነ ሕግን ለመቅጥር ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት ተመዝግባችሁ መስፈርቱን ያሟላችሁ ተወዳዳሪዎች የካቲት 25/2016 ዓ.ም የጽሁፍ ፈተና እንድትፈተኑ መደረጉ ይታወሣል።

የፈተና ውጤት ከዚህ በታች የተገለፀ ሲሆን በፈተናው ውጤት ላይ ያላችሁን ቅሬታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 (ሶስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ (እስከ ሚያዝያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ) ለዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት እንድታቀርቡ እየገለጽን የፈተና ውጤታችሁ 50 እና ከ50 በላይ የሆነ ተወዳዳሪዎች፣ 45 እና ከ45 በላይ የሆነ ሴት ተወዳዳሪዎች እና 45 እና ከ45 በላይ የሆነ አካል ጉዳተኛ ተወዳዳሪዎች ፈተናውን ያለፋችሁ ሲሆን ሚያዝያ 07 እና 08 ቀን 2016 ዓ.ም የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡

የዐቃብያነ ሕግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ ጽ/ቤት

Tagged Under: addis ababa • Announcement • appeal • appeal period • applicant • attorney • calendar • eligibility criteria • Ethiopian Calendar • exam • Government Job • grade • Job Announcement • legal counsel • Legal Profession • office • period • Prosecution • Prosecutor • public • public-prosecutor-office • Recruitment • results • written • written exam results
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች