እድሜው 72 ዓመት የሆነው ተስፋዬ ደመቀ ተ/ማርያም የተባለው ተከሳሽ ከእሱ ጋር ተቃራኒ ጾታ ካላት እና እድሜዋ 13 ዓመት ካልሞላት ህፃን ልጅ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ለመፈፀም አስቦ በቀን 14/12/2016 ዓ.ም ከረፋዱ በግምት 05፡00 ሰዓት ሲሆን በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላ ዶክተሮች ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ እድሜዋ 4 ዓመት የሆናትን ህፃን ከምትኖርበት ቤት ግቢ ወጥታ ቆማ እያለ ተከሳሹ የጥበቃ ስራ ወደሚሰራበት ግቢ ነይ እንጫወት በማለት እጇን ይዞ ከወሰዳት በኋላ ወደሚተኛበት ክፍል ይዟት በመግባት በሩን ዘግቶ የግብረስጋ ግንኙነት ሊፈፅምባት ሲል ህፃኗን በመፈለግ ላይ የነበረችው የግል ተበዳይ አክስት በሩን ከፍታ ገብታ ሁኔታውን ስትመለከት ባሰማችው የድረሱልኝ ጩኸት በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ደርሰው ለፖሊስ በማሳወቅ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ ምርመራ ተጣርቶ በፍትሕ ሚኒስቴር የቦሌ ቅርንጫፍ ዐቃቢ ሕግ በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለቦሌ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሽ ላይ በ1997 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1) እና 27(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በህፃን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት በደል ሙከራ ወንጀል ክስ መስርቶ ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
በክርክሩ ሂደትም የዐቃቢ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ ተከሳሽ የመከላያ ማስረጃ የለኝም በማለት ለፍ/ቤቱ የገለፀ ሲሆን ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ በመስጠት ተከሳሹ በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡