የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራሉ መንግሥት አባል ክልሎች፣ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መርጠው በሚልኳቸው አባላት የተመሠረተ በመሆኑ፤
ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥቱ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውን እንዲሁም አፈ ጉባዔው በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 66 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት የምክር ቤቱን የአስተዳደር ሥራዎች አቀናጅቶ ለመምራት እንዲችል የምክር ቤቱን ጽሕፈት ቤት እንደገና ማቋቋም በማስፈለጉ፤
የሚቋቋመው ጽሕፈት ቤት ምክር ቤቱን በብቃት እንዲያገለግል አድርጎ ማቋቋምና ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ የሚያስችል የራሱ አደረጃጀት፣ አሠራርና በቂ የሰው ኃይል ሊኖረው የሚገባ መሆኑን በማመን፣
በጽሕፈት ቤቱ አደረጃጀትና አሠራር ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመሙላት ምክር ቤቱ ከደረሰበት ተቋማዊ የእድገት ደረጃ ጋር በሚመጥን መልኩ ተልዕኮውን እንዲያከናውን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•