ለኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ልማት የዋጋ መረጋጋት እና ጤናማ የፋይናንስ ሥርዓት ኣስፈላጊ በመሆኑ፤
በፋይናንስ ዘርፉ ውስጥ በየጊዜው ከሚኖሩ ለውጦች ጋር በሚጣጣም መልኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ሥልጣን እና ተግባራት እንደገና በመወሰን የቁጥጥር አቅሙን ማጎልበት አስፈላጊ በመሆኑ፤
ተጠያቂነት፣ ግልጸኝነት እና አስተዳደር ከዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ማጠናከር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 61 ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•