የኤክሳይዝ ታክስ የተጣለባቸውን ዕቃዎች ዓይነት እንደገና በመፈተሽ በትክክል የቅንጦት ዕቃዎች ናቸው በሚባሉ፣ የኅብረተሰቡን ጤና በሚጎዱ እና የማኅበራዊ ችግር በሚያስከትሉ እንዲሁም መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች እኖና አገልግሎቶች ላይ እንዲጣል ማድረግ በማስፈለጉ፤
በማምረቻ ወጪ ላይ ሲሰላ የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ በፋብሪካ የመሸጫ ዋጋ እንዲተካ መደረጉ ታክስ ከፋዮች ሊከፍሉት በሚገባ ታክስ ተገማችነት ረገድ ሲያጋጥማቸው የነበረውን ችግር የሚያቃልል መሆኑ ስለታመነበት፤
በሥራ ላይ የነበረው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ባሉበት ጉድለቶች ምክንያት የኤክሳይዝ ታክስን በትክክል በመሰብሰብ ረገድ ያጋጠመውን ችግር መቅረፍ የሚያስችል አዋጅ ማውጣት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሚክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•