የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ፣ የልማት ሃሣብ ንድፍ ሲዘጋጅ ቦታው ሲመረጥ፣ ሲገነባ ወይም ሲተገበር እንደዚሁም በመተግበር ላይ ያለ እንቅስቃሴ ሲሻሻል ወይም ሲቋረጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ በመተንበይና አስቀድሞ በማረም በውል የታሰበበትን ልማት ለማምጣት የሚያግዝ በመሆኑ፣
መንግሥታዊ ሰነድ በአካባቢ ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን ተፅዕኖ ለመለየት ገና ከመፅደቁ በፊት መገምገም፣ የመፅደቂያው ውሳኔ በሚሰጥበት ወቅት አካባቢያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና ማህበራዊ ታሳቢዎችንና ግቦችን ዘላቂ ልማትን ለማምጣት በሚያመች ሁኔታ እንዲዋሃዱና እንዲቀናጁ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ፣
አሉታዊ የአካባቢ ተፅዕኖዎችን መተንበይ የመፍትሔ እርምጃዎችን መውሰድና ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቃሚነታቸውን ማዳበር በሕገ መንግሥት የተደነገጉትን የአካባቢ ደህንነት መብቶችንና ዓላማዎችን የመተግበርን ሂደት የሚያግዝ በመሆኑ፣
የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አስተዳደራዊ ግልፅነትና በኃላፊነት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ፣
በአጠቃላይ ራሱንና አካባቢውን በሚመለከቱ የልማት እቅዶች አወጣጥና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሕዝቡን፣ በተለይም ደግሞ ማሕበረሰቦችን ለማሳተፍ የሚረዳ በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•