የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ የልማት ሀሳብ ንድፈ ሲዘጋጅ ፣ ቦታው ሲመረጥ ፣ ሲገነባ ወይም ሲተገበር አንደዚሁም በመተግበር ላይ ያለ እንቅስቃሴ ሲሻሻል ወይም ሲቋረጥ የሚያስከትለዉን ተፅዕኖ በመተንበይና አስቀድሞ በማረም በዉል የታሰበዉን ልማት ለማምጣት የሚያግዝ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ፣
መንግስታዊ ሰነድ በአካባቢና ማኅበረሰብ ሊያስከትከል የሚችለዉን ተፅዕኖ በመለየት ከመፅደቁ በፊት በመገምገም ፣ የማፅደቅያው ዉሳኔ በሚሰጥበት ወቅት አካባቢያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ባህላዊና ፣ማኅህበራዊ ታሳቢዎችን እና ግቦችን ዘላቂ ልማት ለማምጣት በሚያመች ሁኔታ አንዲወሃዱ እና እንዲቀናጁ ለማድረግ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ፣
ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ከደረሰችበት የኢኮኖሚ እድገት አኳያ የልማት እንቅስቃሴ በአካባቢ፣ በማኅበረሰብ እና በኢኮኖሚ የሚያሰድሩትን አሉታዊ ተፅዕኖ ቢቻል ለማስቀረት ወይ ለመቀነስ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ፣
አሉታዊ የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖዎችን መተንበይ፣ የመፍትሄ እርምጃዎችን መውሰድና ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቃሚነታቸዉን ማዳበር፣ በሕገ መንግስት የተደነገጉትን የአካባቢ ደህንነት መብቶችንና ዓላማዎችን የመተግበርን ሂደት የሚያግዝ በመሆኑ፣
የአካባቢና ማኅበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ አስተዳደራዊ ግልፅነት፣ ኃላፍነት እና ተጠያቅነት እንዲኖር ለማድረግ፣ በአጠቃላይ እራሱንና አካባቢዉን በሚመለከቱ የልማት ዕቅዶች አወጣጥና ዉሳኔ አሰጣጥ ላይ ሕዝቡን ፣ በተለይም ደግሞ ማኅበረሰቡን ለማሳተፍ የሚረዳ በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት በአንቀፅ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታዉጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•