በአገልግሎት ላይ

ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

መንግስት ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ የመከላከልና የመጠበቅ፣ የሀገርን ሰላምና ደህንነት የማስከበር እና የህዝቦችን አንድነትና እኩልነት እውን በማድረግ የዜጎች በነፃነት የመዘዋወር፣ በመረጡት ቦታ የመኖርና ሀብት የማፍራት ህገመንግስታዊ መብታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን በመገንዘብ፤

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ሕገ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን፣ የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚጥስና ለአደጋ የሚያጋልጥ ብሎም የህዝቦች በአንድነት አብሮ የመኖር እሴትን የሚንድ፣ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የስራ እንቅስቃሴን የሚያስተጓጉል፣ የህግ የበላይነትን የሚያዳክም፣ በምትኩ ደግሞ በሀይል የታገዘ ሁከትና ብጥብጥ እንዲሁም ሥርዓት አልበኝነትን የሚያነግስ፣ የበርካታ ንፁሀን ሰዎችን ህይወት ያጠፋና ብሄርን መሰረት ያደረገ ጥቃት እየተፈፀመና የህዝቦች መፈናቀል እየደረሰ፣ የሀገራችን ኢኮኖሚ እየተጎዳ፣ ንብረት እየወደመ፣ የህዝቡ በሰላም ወጥቶ መግባት እየታወከ እንዲሁም ይህ ሁኔታ እየተስፋፋና እየተራዘመ መሄዱን በመገንዘብ፤

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 2/2010
ቀን: መጋቢት 14፥ 2010 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

582/2018

ታህሳስ 15÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1358/2017

ጥር 29፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1083/2010

መጋቢት 14፥ 2010 ዓ.ም.
የተሻረ