ህገመንግስቱን እና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ የመከላከል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀ በመሆኑ፣
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕገመንግስቱ አንቀፅ 93 (2) (ለ) መሰረት በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ ያለበት በመሆኑ፣
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያፀደቀው በመሆኑ፣
በኢትዮጵያ ፌደራሊዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 93 (2) (ለ) እና አንቀፅ 55 (8) መሰረት የሚከተለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።
•