የሀገሪቱን የኢኮኖሚ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘላቂነት እንዲኖረው ለማድረግ እና ለግል ኢንቨስትመንት አመቺ የሆነ የፖሊሲ ከባቢዎችን ለመፍጠር የሕግ ማሻሻያዎች ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የግል ዘርፉ በኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖረውን ሚናና ተሳትፎ ማስፋፋትና ማዳበር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ቅልጥፍና ማሻሻል፣ ተወዳዳሪነታቸውን ማጎልበት፣ ለካፒታል ያላቸውን ተደራሽነት እና የአገልግሎታቸውን ጥራትና ተደራሽነት ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ይህንኑ ዓላማ ከግብ ለማድረስ በሰፊ መሠረት ላይ የተጣለ ይፋና ግልጽ የሆነ የፕራይቬታይዜሽን ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•