በአገልግሎት ላይ

የኢትዮጵያ የሜዳል፣ ኒሻን እና ሽልማት አዋጅ

በሀገራችን በተለያዩ መስኮች የላቀ ሥራ የሰሩ ግለሰቦችን እና ሌሎች አካላትን እውቅና መስጠት ላለው ማሕበረሰብ የነርሱን አርአያ እንዲከተል የሚያበረታታ፣የሥራ ፈጠራ እንዲስፋፋ እና አሁንተናዊ እና ቀጣይነት ያለው ልማት ለማስመዝገብ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች እንዲሁም በምርምር፣ በትምህርት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፣በህክምና፣ በሥነ-ጥበብ፣ በሥነ ጽሁፍ፣ በባህል፣ በአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች ተመሳሳይ ዘርፎች ከአገሪቱ እድገት ተጨባጭ የሆነና የሊቀ ተግባር ለፈጸሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች ክብር እና እውቅና መስጠት ተቀባይነት ያለው አሰራር በመሆኑ፤

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 71 (5) እና አንቀጽ 74 (10) ላይ ኒሻን እና ሽልማትን በተመለከተ የተቀመጡት ድንጋጌዎችን የሚያስፈጽም እና በአጠቃላይ ሀገራዊ የሜዳይ ፣ኒሻን እና ሽልማት አሰጣጥ የሚመራበት ሕጋዊ ሥርዓት መዘርጋት አስፈሊጊ በመሆኑ፣

በኢትዮጵያ ፌዴራሊዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሉክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1325/2017
ቀን: መስከረም 7፥ 2017 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

No data was found