የተሻረ

የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ማፅደቂያ አዋጅ

ስለደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም የወጣ አዋጅ ደን የማልማት፣ የመጠበቅና ዘላቂነት ባለው መልኩ የመጠቀም ተግባር የሕብረተሰቡን የደን ውጤቶች ፍላጎት ለማሟላትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ባጠቃላይ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ፤

የሀገሪቱን የደን ሀብት ዘላቂነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል የሚቻለውም ከመንግሥት ጎን ለጎን የህብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎና የጥቅም ተካፋይነት ሲረጋገጥ እንዲሁም የደን ፖሊሲና ፕሮግራም ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች በተለይም ከግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ ጋር ሲጣጣም በመሆኑ፤

በከፍተኛ ደረጃ ጎልቶ በሚታየው የሀገሪቱ ደን መመናመን ምክንያት እየተከሰተ ያለውን የአፈር መከላት፣ የበረሃማነት መስፋፋት፣ የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት፣ የብዝሐ ሕይወት መመናመንና የግብርና ምርት ማሽቆልቆል ለመግታት የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ፤

በዚህም መሠረት የደን ልማትን ለማበረታታትና ውሱን የሆነውን የሀገሪቱን የደን ሀብት በአግባቡ ለመጠበቅና ለመጠቀም ስለደን ጥበቃ፣ ልማትና አጠቃቀም አዲስ ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤

መሬትንና የተፈጥሮ ብትን ለማስተዳደር ለክልሎች የተሰጠው ሥልጣን በሥራ ላይ የሚውለው የፌዴራል መንግሥቱ በሚያወጣው ሕግ መሠረት መሆኑን የሕገ-መንግሥት አንቀጽ 52 ንዑስ አንቀጽ 2(መ) ስለሚደነግግ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፤

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 542/1999
ቀን: ነሐሴ 29፥ 1999 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 605/2001

•

ኅዳር 24፥ 2001 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 481/1998

•

የካቲት 20፥ 1998 ዓ.ም.
አዋጅ ቁጥር 288/1994

•

ሰኔ 30፥ 1994 ዓ.ም.
የተሻረ