የኢኮኖሚ እድገትን እና የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለንግድ ሥራ ጽኑ የሕግ መሠረት መጣል የግድ ይላል፡፡ በ 1922 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ለዚህ ዓላማ ከግብ መድረስ አስፈላጊውን መደላድል የሚያኖር ነበር፡፡ ከዘመኑ የኢትዮጵያ የዕድገት ደረጃ አኳያ ሲታይ ከጊዜው እጅግ የቀደመ ነበር ማለትም ይቻላል፡፡
ሆኖም ሕጉ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባለፉት ስልሳ ዓመታት ብዙ ነገሮች ተለውጠዋል፡፡ ንግድ እና የመዋዕለንዋይ ፍሰት እጅግ ከመጨመራቸውም በላይ እያደር ድንበር ዘለል ባህሪ እየተላበሱ መጥተዋል፡፡ እነዚህ ክስተቶች በተለይ ኢትዮጵያ ገበያ መር ሥርዓት መከተል ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ሕጉ በተግባር እንዲፈተሸ ዕድል ፈጥረዋል፡፡
በመሆኑም ሕጉ ውስጥ አንዳንድ ክፍተቶች እና ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ ለአፈጻጸም የማይመቹ እና ለተለያዩ ትርጉሞች የተጋለጡ ብዙ ድንጋጌዎች እንዳሉበትም ግልጽ ሆኗል፡፡ በአጭሩ ለመጪዎቹ አስርት ዓመታት የንግድ እንቅስቃሴን ለመምራትና ለመግዛት ቀርቶ ዛሬ ኢትዮጵያ ለደረሰችበት የኢኮኖሚ እንቅስቀሴ ደረጃም ቢሆን ሕጉ የተሟላ እና በቂ ሆኖ አልተገኘም፡፡
ስለዚህ የነጋዴዎችን፣ የባለሀብቶችን እና በሕጉ ጥቅማቸው በቀጥታ የሚነካ ባለድርሻ አካላት መብቶችን በሚዛናዊ ሁኔታ ለማስተናገድ ፤ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማረጋገጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማስፋፋት ብሎም የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ የንግድ ሕጉን ዘመናዊ ማድረግ የግድ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (4) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•