በአገልግሎት ላይ

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ

የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ፍትሀዊ፣ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ በማድረግ የንግዱን ማህበረሰብ እና ህብረተሰቡ ከንግዱ ሥርዓት የሚጠብቀውን አገልግሎት እንዲያገኝ የሕግና የአሠራር ክፍተቶችን በመድፈንና እርካታን በማሳደግ በአገሪቱ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚ ውስጥ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ማድረግ በማስፈለጉ፤

የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ አሰጣጥን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ የንግድ ሥርዓቱ ለመረጃ አያያዝ አመቺ እንዲሆን፣ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ለመግታት የሚያስችል፣ ለመንግስት፣ ለህብረተሰብ እና የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ በማስፈለጉ፤

የንግድ ሥርዓቱ ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት በማድረግ የአገሪቱን ራዕይ ለማሳካት እንዲቻል አገሪቱ ዘመናዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ሕግ እንዲኖራት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 980/2008
ቀን: ሐምሌ 29፥ 2008 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

ደንብ ቁጥር 461/2012

ጥር 12፥ 2012 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1152/2011

ነሐሴ 3፥ 2011 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 392/2009

ህዳር 29፥ 2009 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ