በአገልግሎት ላይ

ለብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ሥርዓት ማስፋፊያ ፕሮጀክት የሚውል ብድር ከኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ለማግኘት የተፈረመው የብድር ስምምነት ማፅደቂያ አዋጅ

ለደቡብ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ሥርዓት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል አንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር (ዩ.ኤስ.ዲ 170 ሚሊዮን) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት እና በኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል ሚያዚያ 14 ቀን 2011 በአዲስ አበባ የተፈረመ በመሆኑ፤

ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥቅምት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የፀደቀው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1166/2012
ቀን: የካቲት 24፥ 2012 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች