በሀገራችን የሚካሄዱት የልማት ስራዎች ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ የደን ልማት አያያዝና አጠቃቀምን የሚያረጋግጡ በማድረግ የታቀደውን ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት ስትራተጂ ግብን ለማሳካትና ሀገራችን ከተፈጥሮ ሀብቶቿ ተገቢውን ጥቅም እንድታገኝ ማስቻል በማስፈለጉ፤
ለአካባቢና ለደን ምርምር ሥራዎች ትኩረት በመስጠት የሀገሪቱን ከፍተኛ ተጠቃሚነት በሚያረ ጋግጥ ሁኔታ በተቀናጀና በአንድ ወጥ የምርምር ሥርዓት ውስጥ ማደራጀት በማስፈለጉ
መንግሥት ለአካባቢ ጥበቃ፡ ለደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ሥራዎች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የአካባቢና ደን ሚኒስቴርን ያቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት የደን ምርምርን ከአባባቢ ጥበቃ ምርምር ጋር በኢንስቲትዩት ደረጃ ማስተሳሰር በማስፈለጉ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 691/2003 (በአዋጅ ቁጥር – 803/2005 እንደተሻ ሻለው) አንቀጽ 5 እና 35 መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡
•
•
•
•
•