በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በጣሊያን ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል እኤአ ኤፕሪል 8 ቀን 1997 ሮም ላይ የባህል ትብብር ስምምነት የተፈረመ በመሆኑ፤
ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው ተዋዋዮቹ ሀገሮች በየሕገመንግሥታቸው ሥርዓት መሠረት አስፈላጊውን በማሟላት ስምምነቱን ካጸደቁና የማረጋገጫውን ሰነድ ልውውጥ አዲስ አበባ ላይ ካደረጉ ከስድሳ ቀን በኋላ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተመለከተ በመሆኑ፤
ይህንኑ የትብብር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 26 ቀን 1990 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•