የፌደሬሽን ምክር ቤት የፌደራሉ መንግሥት አባል ክልሎች፣ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መርጠው በሚልኳቸው አባላት የተመሠረተ በመሆኑ፤
ምክር ቤቱ በሕገ-መንግሥቱ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በአግባቡ እንዲያከናውንና ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንዲሁም አፈ-ጉባኤው በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 66(2) የምክር ቤቱን የአስተዳደር ሥራዎች አቀናጅቶ ለመምራት እንዲችል የምክር ቤቱን ጽሕፈት ቤት ማቋቋም በማስፈለጉ፤
የሚቋቋመው ጽሕፈት ቤት ምክር ቤቱንና የሕገ-መንግሥት አጣሪ ጉባኤውን በጋራ እንዲያገለግል አድርጐ ማቋቋምና ሁለቱም አካላት ኃላፊነታቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያስችል የራሱ አደረጃጀት፣ አሠራርና በቂ የሰው ኃይል ሊኖረው የሚገባ መሆኑን በማመን፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•
•
•
•
•