በአገልግሎት ላይ

የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ማስፈጸሚያ የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ

ኢትዮጵያ በአብዛኛው አካባቢዎቿ ተመጣጣኝ የሆነ ዝናብ የምታገኝና በርካታ የሀገር ውስጥና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ባለቤት ብትሆንም ይህንን ሀብት የዜጎችን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአግባቡ ያልተጠቀመችበትና በቀጣይ በምታካሂደው ልማት የሕዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆኑ፤

የጋራ ዕቅድ፣ የተናበበ አተገባበር፣ ጠንካራ ክትትልና ግምገማ እንዲኖር በማድረግ በክልሎች ወይም በዘርፎች መካከል የሚከናወኑ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውጤታማና ዘላቂነታቸውን ማረጋገጥ ተገቢ በመሆኑ፤

የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም፣ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት፣ ዘላቂ ልማትን ማስፋፋት፣ የተፈጥሮ ሥነ ምህዳርን መጠበቅ፣ የውሃ ሀብት መጠንንና ጥራትን ማረጋገጥ፣ በአጠቃላይ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን መተግበር የሁሉንም አካላት ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ፤

የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ማስፈጸሚያ የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት መቋቋሙ አግባብነት ባላቸው አካላት ዘንድ የተቀናጀ ውጤታማ አመራርና አሰራር በመፍጠር የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፖሊሲን ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ ማድረግ የሚያስችል በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ (፩) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1375/2017
ቀን: ግንቦት 5፥2017 ዓ.ም.
Law Type: proclamation

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

589/2018

ሚያዝያ 20÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ

በአገልግሎት ላይ
1401/2018

ሚያዝያ 13÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1401/2018

ሚያዝያ 13÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ