የኢኮኖሚ ወንጀል በሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ይህንን ወንጀል መከላከል እና መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ እና ማንኛውም ሰው ከሕገ ወጥ ድርጊት ማንኛውንም ዓይነት የኢኮኖሚ ጥቅም ማግኘት እንዳይችል የሚያደርግ ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በወንጀል የተገኘ ንብረትን ማጥናት፣ መለየት ማገድ፣ መክሰስ፣ ንብረት ማስተዳደር እና መውረስን የሚመለከቱ በተለያዩ ሕጎች ተበታትነው የሚገኙ ድንጋጌዎች በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ በማምጣት እና ለሁሉም የወንጀል ዓይነቶች እንዲያገለግሉ በማድረግ ለመሠረታዊ የሕግና የእፈፃፀም ጥያቄዎች ወጥነት ያለውና በቂ መልስ የሚሰጥ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
ምንጩ ያልታወቀ ንብረት በሃገሪቱ የግብር ሥርዓት፣ የውጭ ምንዛሬ የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ በመሆኑ እና ያለው የሕግ ማዕቀፍ በመንግስት እና በህዝባዊ ድርጅት ሠራተኞች ላይ ብቻ የተወሰነ በመሆኑ ችግሩን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የተሟላ የሕግ ማዕቀፍ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
ኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስን በተመለከተ ያፀደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በተግባር ለማስፈፀም እና በወንጀል ድርጊት የሚገኝ ንብረትን ማስመለስ፣
መውረስና ማስተዳደርን በተመለከተ ዓለም አቀፍ መለኪያዎችን የሚያሟላ የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ በማስፈለጉ፣
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•