በአገልግሎት ላይ

የንብረት ማስመለስ አዋጅ ቁጥር 1364/2017

የኢኮኖሚ ወንጀል በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ ይህንን ወንጀል መካከል እና መቆጣጠር አስፈላጊ በመሆኑ እና ማንኛውም ሰው ከሕገ-ወጥ ድርጊት ማንኛዉንም ዓይነት የኢኮኖሚ ጥቅም ማግኘት እንዳይችል የሚያደርግ ሥርዓት በሕግ መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ማጥናት፤ መለየት፤ማገድ፤መያዝ፤መመርመር፤ መክሰስ፤ንብረት ማስተዳደር እና መዉረስን የሚመለከቱ በተለያዩ ህገች ተበታትነው የሚገኙ ድንጋጌዎች በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ዉስጥ በማምጣት እና ለሁሉም የወንጀል ዓነቶች እንዲያገለግሉ በማድረግ ለመሠረታዊት የሕግና አፈፃፀም  ጥያቄዎች ወጥነት ያለውና በቂ መልስ የሚሰጥ ሕግ ማዉጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ምንጩ ያልታወቀ ንብረት በአገሪቱ የግብር ሥርዓት፤ የዉጭ ምንዛሬ፤ የገንዘብ ዝዉዉር ሥርዓት እና የዉጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደር  በመሆኑ እና ያለው የሕግ ማዕቀፍ በመንግሥት እና በሕዝባዊ ድርጅትሠራተኞች ላይ ብቻ የተወሰነ በመሆኑ ችግሩን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል የተሟል የሕግ ማዕቀፍ ማዉጣት አሰፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ኢትዮጵያ በወንጀል የተገኘ ንብረት ማስመለስን በተመለከተ ያጸደቀቻቸውን ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች በተግባር ለማስፈጸም እና በወንጀል ድርጊት የሚገኝ ንብረትን ማስመለስ፤ መዉረስና ማስተዳደርን በተመለከተ ዓለም ዓቀፍ መለኪያዎችን የሚያሟላ የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር  ማድረግ በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታዉጇል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF
መለያ: አዋጅ ቁጥር 1364/2017
ቀን: ሚያዚያ 24፥ 2017 ዓ.ም.
Law Type: Proclamations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

589/2018

ሚያዝያ 20÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ

በአገልግሎት ላይ
1401/2018

ሚያዝያ 13÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1401/2018

ሚያዝያ 13÷2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ