ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ባጸደቀችው የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ 43 (2) ላይ፣ በኮንቬንሽኑ አባል ሀገሮች ጉባዔ እ·ኤ·አዲሴምበር 12 ቀን 1995፣ የተደረገውን ማሻሻያ ከደገፉት አንዷ በመሆኗ፤
በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ እ·ኤ·አ ዲሴምበር 21 ቀን 1995 ተቀባይነት የተሰጠው ማሻሻያ የሚጸናው፣ ከኮንቬንሽኑ አባል ሀገሮች ሁለት ሦስተኛው በኮንቬንሽኑ አንቀጽ 50 (2) መሠረት ሲያጸድቁት ጭምር ስለሆነ፤
ይህንኑ ማሻሻያ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 17 ቀን 1990 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ።
•
•
•
•
•