ወደአገር ውስጥ ለሚገቡ ዕቃዎች ለተከፈለው የውጭ ምንዛሪ ተመጣጣኝ የሆነ ዕቃ መገኘቱን ማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
ለንግዱ እንቅስቃሴ ፈጣንና አመቺ ሁኔታን ለመፍጠር የጉምሩክ ፎርማሊቲን አፈጻጸም ሥርዓት በቅድመ ጭነት ምርመራ መርዳት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት፡
ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ዕቃዎች ዓይነት፡ ጥራት፡ ደረጃ እና ብዛት በግዢው ውል በተዘረዘረው መሠረት መሆኑን ዕቃው ከመጫኑ በፊት ማረጋገጥ ክፍያ ከተፈጸመ በኋላ የሚያጋጥመውን ውጣ ውረድ በማስቀረት ዕቃዎች በተፈለገው ጊዜ ሥራ ላይ እንዲውሉ የሚያስችል መሆኑን በመረዳት፣
የዕቃዎችን ዋጋ በማሳነስ በመንግሥት ገቢ ላይ የሚፈጠ ረውን ችግር ለማስወገድ የቅድመ ጭነት ምርመራ አጋዥ ስለሚሆን፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመን ግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።
•
•
•
•
•