የገጠር የፋይናንስ አገልግሎትንና ተቋምን ለማሳደግ የሚረዳ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል መጠኑ 27 ሚሊዮን 170 ሺ ዩ.ኤ. (ሃያ ሰባት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰባ ሺ ዩኒትስ ኦፍ አካውንት) የሆነ ገንዘብ የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 13 ቀን 2013 በቱኒስ የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 18 ቀን 1996 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55(1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•