የተሻረ

በአስቸኳይ ጊዜ ደንብና መመሪያዎች ላይ የተመለከቱ የትራፊክ ጥሰቶች በተፈጸሙ ጊዜ የሚጣሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶች መወሰኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

በአስቸኳይ ጊዜ ደንብና መመሪያዎች መሰረት ከትራንስፖርት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ክልከላዎችና ግዴታዎች የተጣሉ ሲሆን እነዚህ ክልከላዎችና ግዴታዎች በተጣሱ ጊዜ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አንቀፅ 6 መሰረት የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ቢሆንም እነዚህን ክልከላዎችና ግዴታዎች የተላለፉ ሁሉንም ሰዎች በወንጀል ተጠያቂ ማድረግ በፍትህ ስርአቱ ላይ ጫና የሚያሣድር በመሆኑ አስተዳደራዊ ቅጣት መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በመንገድ ትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ደንብ  208/2003 እና ደንብ (ማሻሻያ)ቁጥር 305/2009 ላይ የትራፊክ ደንብ በተጣሰ ጊዜ የሚያስከትለው አስተዳደራዊ ሀላፊነት የተመለከተ ሲሆን እነዚህ ሀላፊነቶች በአስቸኳይ ጊዜ ደንብና መመሪያዎች ላይ የተከለከሉ ተግባራትንና የተጣሉ ግዴታዎችን ሙሉ ለሙሉ የማይሸፍን ከመሆኑም በተጨማሪ ቅጣቶቹም ቢሆን አስተማሪ ባለመሆናቸው ይህንን ደንብ ለተወሰነ ጊዜ በማገድ ከተመለከቱ ክልከላዎችና ከተጣሉ ግዴታዎች ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አስተዳደራዊ ቅጣት መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012አንቀጽ 4 መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: ደንብ ቁጥር 469/2012
ቀን: ሰኔ 4፥ 2012 ዓ.ም.
Law Type: Regulations

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

አዋጅ ቁጥር 1374/2017

ሰኔ 11፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 566/2016

ጥር 30፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 563/2016

ጥር 16፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 560/2016

ጥቅምት 19፥ 2017 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1333/2016

ጷጉሜ 4፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1338/2016

ሐምሌ 25፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 552/2016

ሐምሌ 9፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 547 /2016

ግንቦት 22፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
ደንብ ቁጥር 545/2016

ግንቦት 15፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1307/2016

ጥር 7፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
አዋጅ ቁጥር 1294/2015

መስከረም 25፥ 2016 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ