በአገልግሎት ላይ

የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ የወጣ አዋጅ

የንግድ ሥራ አገሪቱ በምትከተለው የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት ተገቢውን አሠራር ተከትሎ መካሄድ ያለበት በመሆኑ፤

የንግዱን ህብረተሰብ ከፀረ ውድድር እና ተገቢ ካልሆኑ የገበያ ተግባራት፣ እንዲሁም ሸማቹን ከሚያሳስቱ የገበያ ሁኔታዎች የሚከላከልና ለነፃ ገበያ ውድድር አመቺነት ያለው ሥርዓት ማስፈን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የንግድ እንቅስቃሴዎች ማደግን ተከትሎ የሸማቾችን ጤንነትና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የንግድ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን መስፋፋት ለመግታት እንዲቻልና ደህንነታቸውንና ለጤና ተስማሚ መሆናቸውን በዘላቂነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ተጠቃሚዎች ላወጡት ዋጋ ተመጣጣኝ የሆኑ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት በማስፈለጉ፤

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ስርዓት ተፈፃሚነትን ለማረጋገጥ የአስፈፃሚነት በተለይም የመመርመር የመክሰስ እና የዳኝነት ተግባራትን የሚያከናውኑ አካላትን ስልጣንና ተግባር መወሰን – አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጃል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 813/2006
ቀን: መጋቢት 12÷ 2006 ዓ.ም.
Law Type: proclamation

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

1434/2018

ሐምሌ 23÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1425/2018

ሐምሌ 16÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1426/2018

ሐምሌ 14÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
592/2018

ሐምሌ 3÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ