በአገልግሎት ላይ

የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

ነዳጅ ውጤቶች ካላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ አንጻር ስትራቴጂክ ምርቶች በመሆናቸው አቅርቦታቸው፣ ክምችታቸው፣ ስርጭታቸው፣ ደህንነታቸው፣ ጥራታቸው እና ዋጋቸው ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በጠበቀ እና በሰውና በእንስሳት ጤና፣ በንብረትና በአካባቢ ላይ ጉዳት በማያደርስ ሁኔታ መከናወኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤

ከአስመጪው ጀምሮ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ ድረስ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ አስተማማኝ፣ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የአቅርቦት፣ የስርጭት እና የችርቻሮ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት በነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሰንሰለት ውስጥ እየታዩ ያሉ ሕገ-ወጥ ተግዳሮቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በዘርፉ የተሰማሩ የነዳጅ ተቋማትና ባለሙያዎች ዓለም አቀፍ ልምድ በሚጠይቀው መሠረት በሚፈለገው የብቃት ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ደህንነቱ የተጠበቀና ሕጋዊ የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓት ለማስፈን የላቀ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 327(45) መሠረት የሚከተለው ታውጇል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መለያ: አዋጅ ቁጥር 1383/2017
ቀን: የካቲት 24÷ 2017 ዓ.ም.
Law Type: proclamation

ሕጉን ያውርዱ

ተዛማጅ ሕጎች

1434/2018

•

ሐምሌ 23÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1425/2018

•

ሐምሌ 16÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
1426/2018

•

ሐምሌ 14÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ
592/2018

•

ሐምሌ 3÷ 2018 ዓ.ም.
በአገልግሎት ላይ