የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 በመቋቋሙና ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለያየ ተቋም የነበረውን የወንጀል ምርመራ መዝገብ የማቋረጥና የመዝጋት እንዲሁም የክስ መዝገብ የማንሳትና የማንቀሳቀስ አሠራር ከአዲሱ ተቋም ጋር አብሮ በሚሄድ መልኩ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤
በ2003 ዓ.ም የወጣው የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ፖሊሲ የወንጀል ምርመራ መዝገብ የሚቋረጥበትንና የሚዘጋበትን እንዲሁምየክስ መዝገብ የሚነሳበትን ሥርዓት ጠቅላላ መርሆዎች የሚያስቀምጥ በመሆኑና ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ ዝርዝር መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤
የወንጀል ምርመራ መዝገብ የሚቋረጥበትና የሚዘጋበት፣ ክስ የሚነሳበት ሥርዓት ወጥ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ለማስቻል፣ እንዲሁም ሂደቱ ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ እና በቂ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ በማስፈለጉ፤
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 21(2) መሠረት ይህን
መመሪያ አውጥቷል፡፡