በአዲስ አበባ ከተማ በተቋቋመው ማህበረሰብ አቀፍ የፍትህ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለሚያገለግሉ ሽማግሌዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Training Provided to Elders Serving at Community-Based Justice Service Center Established in Addis Ababa

በአዲስ አበባ ከተማ በተቋቋመው ማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለሚያገለግሉ ሽማግሌዎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በአዲስ አበባ እየተሰጠ ይገኛል።

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፍትሕ ቢሮ ህንፃ ላይ የተከፈተው የማኅበረሰብ ፍትሕ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የሚያግዙ ሰራተኞች መቀጠራቸውንና ይህንኑ ተከትሎ አገልግሎቱን ለማስጀመር ሽማግሌዎች በባህላዊ መንገድ ግጭቶቹን ሲፈቱ ታሳቢ ማደረግ ያለባቸው ጉዳዮችና ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተገናኘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ለመስጠት ታስቦ ሥልጠናው መዘጋጀቱን በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ የለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኖህ ታከለ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ሃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በበኩላቸው በአገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎትን በማጠናከር ለመደበኛው የፍትሕ ሥርዓት አጋዥ እንዲሆን ለማስቻል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውሰው ሽማግሌዎች ከዚህ ቀደም አለመግባባቶችን ሲፈቱበት የነበረውን መንገድ አስፍቶ በመሄድ የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጡን ከሕዝብ ጋር ማስተሳሰር በማስፈለጉ አገልግሎት መስጫ ማዕከላቱን ተቋቁመዉ ወደስራ መገባቱን ተናግረዋል።

ይህንኑ ስራ ለማጠናከር እንዲያግዝም የአቅም መገንቢያ ሥልጠናው መዘጋጀቱንና ሽማግሌዎችም በመንግሥት ተቋማት ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ተደራሽ በማድረግ የፍትሕ ስራውን ለማሳለጥ የበኩላቸውን የበጎፈቃደኝነት ስራ እንዲወጡ ጠይቀው በዚህ ተግባር ውጤታማነት ላይም በመመስረት እንደ አገር ተደራሽነቱን በማስፉት በሰፊው የሚከናወን መሆኑን ገልፀዋል።

ሥልጠናው በተለይም ማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት በማዕከል ደረጃ በተደራጀ መልኩ ተቋቁሞ ሲሰጥ ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችሉ አሰራሮች እንዴትና በምን መልኩ እንደሚዘረጉ፣ባህላዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን ዘመኑን በዋጀ መንገድ ለመሥራት ምን ምን ነገሮች መካተት እንዳለባቸው ፣በአዲስ አበባ የተቋቋመው ማዕከልስ በየትኛው የባህላዊ ዘዴ ይታያል በሚሉና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ በመሰጠት ላይ ነው።

ሄግ ኢንስቲትዩት እና ደስትኒ ኢትዬጵያ የሥልጠና መድረኩን ጨምሮ የማኅበረሰብ አቀፍ የፍትሕ አገልግሎት ተግባራትን እውን ለማድረግ ድጋፍ እያደረጉ እነዳሉ በመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: ababa addis addis ababa alternative dispute resolution (adr) capacity Capacity Building center civil liberties community-based community-based justice conflict conflict mediation government initiatives human human rights training Justice Justice System Reform Legal Training resolution Rights Service the hague institute for innovation of law traditional Traditional Conflict Resolution Training training workshop
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች