8ኛው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው

The 8th Joint Assembly of the Ministry of Justice and Regional Justice Bureaus is being held in Dire Dawa City

የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ ክብርን ያረጋገጠ ፣ተዓማኒ የፍትሕ ሥርዓት እንገነባለን” በሚል መሪ-ቃል 8ኛው የፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትሕ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ በድሬዳዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ የፍትሕ ዘርፉ ተዋናዮች በዘርፉ የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ወይይት የሚያደርጉበት፣ የጋራ ፈተናዎችን ለመወጣት የሚያቅዱበት እንዲሁም የተሻሉ አፈፃፀሞችን በመቀመር የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ነው፡፡
በጉባኤው መክፈቻ ወቅት በ3 ዓመት የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተቀመጡትን አምዶች መሰረት በማድረግ ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ የህግ ማዕቀፍ፣ የተቋምና የአሰራር ስርዓቶች በመቅረፅ እንዲሁም በፍትሕ ሚኒስቴር የለሙ ቴክኖሎጂ ሲሰተሞች ላይ ልምዶችን በማካፋል፣ የማህበረሰብ አቀፍ ፍትሕ እንዲጎሎብት በተለያዩ ክልሎች ማዕከላትን በማቋቋም እንዲሁም የአስተዳደር ሥነሥርዓት አዋጅ እንዲያወጡ በማገዝ በአገራችን የለውጥ ጉዞ ውስጥ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፣ ፍትሕ እንዲሰፍን፣ የዜጐች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲረጋገጡ ለማድረግ፣ ዘርፈ ብዙ ጥረት በማድረግ ዉጤታማ ሥራዎች ሲሰሩ እንደነበር ተገልጹዋል።
በተያያዘ እንዲሁ የህዝብ ጥቅምን አደጋ ላይ በሚጥሉ የወንጀል ተግባራቶች ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ የመከላከል ስራ መስራት፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የወንጀል ጉዳዮች ማለትም በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መከላከል፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በህገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት፣ በመሰረተ ልማት አውታር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ወዘተ… የፍትሕ ሥርዓቱ ማነቆ መሆናቸዉን በመገንዘብ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራርን በመዘርጋትና ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የመንግሥትና የህዝብ አመኔታን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡
ጉባኤው ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር በቀጣይ ጊዜያት የፍትሕ ስርዓቱን ተአማኒነት በዘላቂነት ለማስቀጠል እንዲሁም በፍትሕ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀሞች፣ በህጎችና እቅዶች አፈፃፀም ግብዓት የሚገኝበትና የተሻለ ውጤት እንዲገኝ የተሞክሮ ልውውጥ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
በጉባኤው የፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ የድሬዳዋ ከተማ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ፣የክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች፣ የክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮች፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መካከለኛ አመራሮች፣ የፌደራ ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳንት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Tagged Under: addis ababa justice bureau • african charter on the rights and welfare of the child • and healthcare administration and control authority • and peoples' region • and peoples' region (snnpr) • assembly • bureau • bureaus • city • Convention on the Rights of the Child • convention on the rights of the child (crc) • dawa • dire • Dire Dawa • dire dawa administration • dire dawa university • ethiopian federal ministry of justice • Ethiopian Ministry of Justice • fdre ministry of justice • joint • Justice • justice bureau • ministry • ministry of trade and regional integration • oromia regional justice bureau • rea • region • Regional • Regional justice • Regional Justice Bureaus
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች