ፍትሕ ሚኒስቴር በዐቃቤያነ ህግ የሙያ ሥነ ምግባር እና ሙያዊነት ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

Ministry of Justice Steps Up Focus on Prosecutorial Ethics and Professionalism

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርትና ሥልጠና ዳሬክቶሬት አዘጋጅነት በሥነ-ምግባርና ሙያዊነት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ለተቋሙ ዐቃብያነ ሕግ መስከረም 30/2018 ዓ.ም መሰጠት ተጀመረ፡፡

ስልጠናው ከተለያዩ የተቋሙ የሥራ ክፍሎች ለተወጣጡ ዐቃብያነ ሕግ የሚሰጥና በዋነኛነት አላማ ያደረገውም ከሥነ-ምግባር እና ከሙያዊነት አንፃር የተለያዩ ጉዳዮች በማንሳት የጋራ ግንዛቤ መፍጠር እንደሆነ ተገልፆል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የሰራተኞቹን እውቀትና ክህሎት ለማሳደግ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን በዚህም በጥናት የተለዩ እንዲሁም በፍላጎት ላይ የተመሰረቱ ሥልጠናዎችን እያዘጋጀ የባለሙያዎችን አቅም የመገንባት ስራ በስፋት እያከናወ የሚገኝ ሲሆን፣ በጥናት ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀው ይህ የሥነ ምግባርና ሙያዊነት ሥልጠና ተቋሙ በሕግ የተሰጡትን ኃላፊነቶች መወጣት እንዲችል ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡

ሥነ-ምግባር እና ሙያዊነት በብዙ መንገድ የሚገናኙና አንዱ በአንደኛው ውስጥ ሆኖ አብረው የሚሄዱ ጉዳዮች በመሆናቸው ሙያ ከእውቀትና ክህሎት ጋር የሚገናኝ ሥነ-ምግባር ደግሞ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚሄድ ጉዳይ መሆኑ ጋር ተያይዞ፣ ዐቃቤ ሕግ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ሙያዊ ክህሎትና ሥነ-ምግባርን አንድ ላይ ይዞ መገኘት የሚጠበቅበት መሆኑ በተለያዩ ማሳያዎች ለሰልጣኞቹ ገለፃ ተደርጓል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በመሰረቱ ለህዝብ አገልግሎት ሰጪ በመሆኑ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ሥልጣን የተሰጠውና በተለያዩ አሰራሮች የሚገዛ አካል ቢሆንም በዋነኝነት ሁል ጊዜም ቢሆን የሚቆመው የህዝብን እና የመንግስትን ጥቅም ከማስከበር ጋር ተያይዞ ፍትሕን ለማረጋገጥ በመሆኑ ባለሙያው በሚፈለገው ደረጃ የተጣለበትን ኃላፊነት መወጣት የሚችለው ሙያዊ ክህሎትና ሥነ-ምግባር ሲኖረው ብቻ መሆኑ በስልጠና በመድረኩ ተወስቷል፡፡

Tagged Under: ali and healthcare administration and control authority attorney ecu ethics ethiopian federal ministry of justice Ethiopian Ministry of Justice fdre ministry of justice federal ethics and anti-corruption commission federal institute of justice and law federal justice and law institute federal ministry of justice financial and economic development ministry government law and justice services sector innovation and technology ministry Justice justice and democracy affairs lawyer legal counsel lis ministry pro profession professional professionalism Prosecutor prosecutorial
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች