ሙያተኝነትን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሔደ

Panel Discussion Held on Professionalism

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት እና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው መድረክ ሙያተኝነትን አስመልክቶ ውይይት ተካሄደ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የንቃተ ሕግ፣ ትምህርት ሥልጠና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ወርቁ መድረኩን ሲያስጀምሩ ተቋሙ እንደ ግብ ከያዛቸው ተግባራት ውስጥ አንዱ ተቋሙን ሙያተኝነት በስፋት የሚንጸባረቅ ተቋም እንዲሆን ማድረግ ነው ካሉ በኋላ ሙያተኝነትን አስመልክቶ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት የፓናል ውይይት መካሄዱን ገልጸው በ2015 ዓ.ም ከተቀጠሩት ዐቃቤያነ ሕግ ጋር የተደረገው ይህ ውይይትም የዚሁ መርሀ ግብር አካል ነው ብለዋል።

በመቀጠልም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ እና ለረዥም ጊዜ የዴንማርክ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና አለም አቀፉ ዐቃቤያነ ሕግ ማህበር ፕሬዚዳንት እና ሴክሬቴሪያት የነበሩት ዶክተር ራስመስ ዋንደል ከሙያዊነት ጋር በተያያዘ አድርገውት የነበሩት ንግግሮች በቪዲዮ ለሰልጣኖች ቀርበው እንዲታደሙት ተደርጓል፡፡

የፓናል ውይይቱን የቀድሞ የፍትሕ ሚኒስቴር ባልደረባና ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት አቶ እሸቱ ወልደሰማያት መርተውታል፡፡

Tagged Under: Amhara Regional State • attorney • Attorney General • building • capacity • Capacity Building • denmark • development • Discussion • ethics • general • gidion timothy • International Association of Prosecutors • judicial reform • legal • Legal Education • Legal ethics • Legal Profession • Legal Training • panel • panel discussion • profession • professional • professional development • professionalism • rule • Rule of Law • Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች