የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ ሕዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም 3ኛ መደበኛ ስብሰባው በማካሄድ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በዚህ መሠረት ቦርዱ ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ አዋጅ 1249/2013 በአንቀጽ 71 (2) እና (6) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የተዘጋጀውን ረቂቅ መመሪያ ከዚህ ቀደም በቦርድ አባላት በተሰጠው አስተያየት መሠረት ማስተካከያ መደረጉን መርምሮ መመሪያውን ማጽደቅ ሲሆን በመመሪያው ላይ ተወያይቶ መመሪያው “የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ አሠራርን እና የቦርዱን ጽሕፈት ቤት ተግባር ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 1/2015” ሆኖ ሥራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡
በቦርዱ የፀደቀው መመሪያ በአጠቃላይ ስድስት ምዕራፎች ያሉት ሲሆን በዋናነት የቦርዱ አጠቃላይ የአሠራር ሥርዓት፣ ለቦርዱ የሚቀርብ ቅሬታ የሚመራበትን ሥርዓት፣ ቦርዱ ለቦርዱ ተጠሪ ከሆኑ አደረጃጀቶችና ከኢትዮጵያ የፌዴራል ጠበቆች ማሕበር ጋር የሚኖረውን የክትትልና የሪፖርት አቀራረብ ሥርዓትን እንዲሁም የቦርዱን ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት የሚደነግግ ነው፡፡
“የጠበቆች አስተዳደር ቦርድ አሠራርን እና የቦርዱን ጽሕፈት ቤት ተግባር ለመወሰን የወጣወን መመሪያ ቁጥር 1/2015” ከዚህ በታች የተመለከተውን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይቻላል፡፡