የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር በመሆን ተቋሙን ሲመሩ ለነበሩት እና በቅርቡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በትላንትናው እለት ሽኝት በማድረግ በአዲሱ የስራ ኃላፊነት ቦታቸው ለሚኖራቸው ጊዜ መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል፡፡
በተያያዘም ተቋሙን ለረዥም ጊዜ ሲያገለግሉ ቆይተው ጡረታ ለወጡ 25 ሰራተኞች የምስጋና መርሀ-ግብር የተካሄደ ሲሆን ሰራተኞቹ በተቋሙ በነበራቸው የስራ ጊዜ ላበረከቱት አገልግሎት የምስጋና የምስክር ወረቀት በክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ አማካኝነት ተበርክቶላቸዋል፡፡