የፍትሕ ሚኒስቴር የተማከለ እና ዲጂታል የፍትሕ አገልግሎት አሠጣጥን እውን ለማድረግ የተገልጋዮች አገልግሎት ሥራውን በተመረጡ ቅርንጫፎቹ መስጠት ጀመረ

Ministry of Justice launches customer services in selected branches to enable centralized, digital justice delivery

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር አዲስ ለተቋቋመው የተገልጋዮች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዕጩ አቃብያነ ሕግን በዘርፉ በማሰልጠን ዋናው መስሪያ ቤትን ጨምሮ በቦሌ፣ለሚ ኩራ፣ አራዳ፣ ልደታ እና ንፋስ ስልክ ቅርንጫፎቹ ላይ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል ላይ ትኩረት በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን፣ የተለመውን ርዕይ ለማሳካት እና የተቋቋመበትን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት ይቻለው ዘንድ በአዲሱ አምስት አመት ስትራቴጂክ ዘመን ያሉበትን የፍትሕ አገልግሎት ውሱንነቶችን ለመፍታት አዲስ አደረጃጀት በመዘርጋት የተገልጋዮች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የሥራ ክፍልን በማቋቋም ተቋሙ የሚሰጣቸውን የፍትሕ አገልግሎቶች በተሻለ ሁኔታ ለመስጠት ዕጩ ዐቃቤያነ ሕግን አሰልጥኖ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የሥራ ክፍሉ በዋናነት በተገልጋዮች አያያዝ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለተገልጋዮች አገልግሎት (Customer Service) መሰረታዊ መርሆዎች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አገልግሎቱን የሚሰጡ ዐቃብያነ ሕግ የአገልግሎት ሰጪው ሚና፣ የሚጠበቁ ሥነ-ምግባራዊ ባህሪያት፣ ሊቀረፉ የሚገቡ የተለመዱ ሥህተቶች እና የተግባቦት ክህሎቶችን በተመለከተ እንዲሁም የተቋሙን አጠቃላይ የኦንላይን አሰራር ሥርዓት፣ የዳይሬክቶሬቱን የሥራ መመሪያ እና አጠቃላይ የሥራ ፍሰቱን የተመለከቱ የተግባር ስልጠናዎችን መስጠት ተችሏል።

አገልግሎት አሠጣጡ በፍትሕ ሚኒስቴር እና በተገልጋዩ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ግልጽ እና ተደራሽ የሚያደርገው ከመሆኑ በላይ፣ በዐቃቤ ሕግ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ በተቋሙ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ላይ በዘርፉ የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩና የሕዝብ አመኔታ የተጣለበት የፍትሕ ሥርዓት በመገንባት ሂደት ውስጥ የተማከለ እና ዲጂታል የፍትሕ አገልግሎት አሠጣጥን እውን ለማድረግ በተቋሙ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን ውጤታማ ለማድረግ የራሱ ድርሻ እንዳለው ይታመናል፡፡

በመሆኑም አገልግሎቱን ለማግኘት ከዚህ በታች የተገለፁትን አማራጮች መጠቀም የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

 የተገልጋዮች አገልግሎት (Customer Service) ኢ-ሜል አድራሻ:- [email protected]

 በነፃ የስልክ ጥሪ (Hotline )- 8797

አገልግሎቱን በቅርንጫፎች ለማግኘት፡-

 ዋናው መስሪያ ቤት፡-0115151771

 ቦሌ፡-0116687843

 ለሚ ኩራ፡-0116702689

 አራዳ፡-0111281150

Relevant Departments and People
Tagged Under: ali branch central customer customer service decentralized service delivery delivery digital digital justice ethiopian federal ministry of justice Ethiopian Ministry of Justice fdre ministry of justice federal civil service ministry federal ministry of justice government law and justice services sector health service delivery hotline Justice justice service delivery launch line live ministry Service Services un vice
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች