የፍትህ ሚኒስቴር የመዝገብ ማጥራትና ውሳኔን አስመልክቶ የውይይት መድረክ አካሔደ

Ministry of Justice Holds Discussion Forum on Case Backlog Reduction and Adjudication

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የመዝገብ ማጥራትና ውሳኔን አስመልክቶ ከክልልና ከተማ መስተዳድር የፍትሕ ቢሮ መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ጋር በአዳማ ከተማ የውይይት መድረክ አካሔደ::

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የክልል ጉዳዮች ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አበራ ከወንጀል መዛግብት ምርመራና ውሳኔ ማሰጠት ፣የክልል ፍትሕ ቢሮ የሀብት ማስመለስ አጠቃላይ መረጃ ፣በክልል ፍትሕ ቢሮዎች የተከናወኑ የሕግ አገልግሎቶች ፣በውክልና የተሰጡ የፌዴራል ጉዳዮች የ2016 በጀት አፈፃፀም ግምገማ ፣የፌዴራል ጉዳዮች ይግባኝ ክርክር መዝገብ ብዛት እና የመዝገብ ማጥራት ውሳኔ በሚሉ ይዘቶች ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም የቀረበውን ገለፃ ተከትሎ ጥያቄና አስተያየት ተነስቷል ፤በዚህም ለቀረቡ ጥያቄዎች በፍትሕ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) እና በአቶ አበራ በኩል ምላሽና ማባራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው በውይይቱ ማጠቃለያ እንዳሉት የትራንስፎርሜሽኑን ዕቅዱ መሠረት ተደርጎ ለክልልና ለከተማ መስተዳደር ፍትሕ ቢሮ አመራሮችና ባለሙዎች የሥልጠና ፣ የምክክር ፣በዕቅዱ ዙሪያ አብሮ መወያየት እና ሌሎችም ስራዎች በጋራ መሰራታቸውን አውስተው በቀጣይ በክልል እና በከተማ መስተዳደር ፍትሕ ቢሮዎች የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አተገባበርን አስመልክቶ ግምገማ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴር በፍትሕ ተቋማት እየታዩ ያሉ ችግሮችንና መሻሻል የሚጠይቁ ጉዳዮችን ተቋሙ ከሌሎች የፍትሕ አካላት ጋር በመተባበር እንዲሁም ራሱ ተቋሙ እያበለፀጋቸው ባሉ እና ከሌሎች አካላት ጋር ተባብሮ እያበለፀጋቸው ባሉ የቴክኖሎጂ አማራጮች በመታገዝ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን እንደሚቀርፍ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ለመድረኩ ተሳታፊዎች የ2017 በጀት ዓመት የስራ አቅጣጫዎችን በዝርዝር አመላክተዋል፡፡

Tagged Under: adama adjudication backlog budget performance review Capacity Building case case backlog reduction case management democratic deputy minister Education federal judicial transformation Justice Justice Sector Reform learning Legal Reforms Legal Services minister of justice reduction Regional Regional Justice Bureaus republic resource allocation skill development technology adoption Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች