የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር እና ፍትሕ ሚኒስቴር እንዲሁም ተጠሪ ተቋሞቻቸው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሂደዋል::
በ2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች ማለትም በደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካማ ቤቶች አድሳትና ግንባታ፣ አቅም ለሌላቸው ቤተሰቦች ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በስፋት በመከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በተያያዘም ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም የመከላከያ ሚኒስቴር እና የፍትሕ ሚኒስቴር እንዲሁም ተጠሪ ተቋሞቻቸው አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ሜትሮፖሊትያን ዩንቨርስቲ አካባቢ አመራሮችና የተቋማቱ ሰራተኞች ባካሄዱት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ -ግብር 10 ሺህ ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን ማሳረፍ መቻላቸው ተመልክቷል፡፡