የፍትሕ ሚኒስቴር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባባር በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ -ግብር ላይ ተሳታፊ ሆኑዋል፡፡
በሃገራችን በአሁኑ ወቅት “የምትተክል አገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የ2016 የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እየተካሄደ እንዳለ ይታወቃል፣ ይህንንም ሃገራዊ ንቅናቄ መነሻ በማድረግ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባባር በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ ባዘጋጀው የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ -ግብር ላይ በፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞትዮስ የተመራ ልዑክ ቡድን ተሳታፊ ሆኑዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በመድረክ ንግግራቸው የአርንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እኛ ካለፍን በዃላ ለመጪው ትውልድ የምናስተላልፈው ትልቅ ሃብት መሆኑን ጠቅሰው ብዙ ከማለት ይልቅ በአሁኑ ወቅት ከኛ የሚጠበቀው ብዙ መትከል ነው በማለት በሀገር ደረጃ በአንድ ጀንበር ብዙ ችግኞችን ለመትከል የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ሁሉም በየደረጃው የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመርሀ-ግብሩም ላይ ፍትሕ ሚኒስቴርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ፣ አባገዳዎች፣ የተለያዩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሃላፊዎችና ተወካዮች፣ የክረምት በጎፈቃደኞች፣ ተማሪዎች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሲሆኑ የዕለቱም መርሃ-ግብር በደማቅ ሁኔታ በተሳታፊዎች የችግኝ ተከላ ሂደት ተጠናቋል፡፡