የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተለያዩ ተግባራትን በማከናወነ መቋጫዉን አግኝቷል፡፡
የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ መርሃ ግብርን በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በመገኘት ሲያከናውኑ የቆዩት የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከ10 ሺህ በላይ ችግኞችን በመትከል፣የከተማ ፅዳት በማከናወን፣የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን ለተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም አምስት የአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታ በማስጀመርና ሌሎች መሰል ስራዎችን በማከናወን በዛሬው እለት ተጠናቋል፡፡