የፍትሕ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በአገር አቀፍ ደረጃ በዛሬው እለት የተካሄደውን በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዬን ችግኞችን የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተከትሎ በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ካራ መድሐኒያለም አቅራቢያ ተገኝተው 12 ሺህ ችግኞችን ተክለዋል።
ከዓመት ዓመት ባህል እየሆነ የመጣውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለትውልድ የሚጠቅም ስራ ለመሥራት ሁሉም የመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች ዘንድሮም በለሚኩራ ተገኝተው እያንዳንዳቸው የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ፍትሕ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የዘንድሮን የክረምት በጎ አድራጎትና የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በመገኘት የተለያዩ በጎ ተግባራትን ማከናወናቸውና 10 ሺህ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች መትከላቸው የሚታወስ ነው።