የህግ አስከባሪ አካላት ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲችሉ የሚያስችል ክህሎት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገለፀ

Ethiopia Strengthens Law Enforcement Capacity to Combat Illegal Human Trafficking and Border Crossing Crimes

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የብሔራዊ ትብብር ጥምረት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብረሃም አያሌው ከሀረሪ ፣ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልል ለተወጣጡ የሕግ አስከባሪ አካላት በተዘጋጀው የሥልጠና መድረክ ላይ ተገኝተው የሕግ አስከባሪ አካላት ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲችሉ የሚያስችል ክህሎት ሊኖራቸው እንደሚገባ በትላንትነው ዕለት በአዳማ ከተማ መካሄድ በጀመረው የሕግ አስከባሪ አከላት የሥልጠና መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡

በሀገራችን በርካታ ሰዎች በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት አካባቢያቸውን ጥለው እንዲፈልሱ እየተደረጉ እንደሆነ የገለፁት ኃላፊው ለዚህም በመተላለፊያና መዳረሻ ሀገራት ለከፍተኛ ስቃይ እንደሚዳረጉ አውስተዋል፡፡

በፍልሰት ጉዳይ በየቀኑ የምንሰማው መረጃ ጉዳዩን በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያመለክት መሆኑን ያወሱት አቶ አብርሃም በመሠረታዊነት እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጣም ብዙ የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉ ተናግረው በዋናነት የችግሩ መነሻ ምክንያት ላይ አተኩሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

አክለውም በኢትዮጵያ ከ95 ፐርሰንት በላይ ፍልሰተኞች የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ብለው እንደሚፈልሱ ጠቁመው የተሻለ የኑሮ ፍለጋ ብለው ወደሌሎች ሀገራት የሚፈልሱት ዜጎች ሀገር ውስጥ ያሉ አማራጮችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማድረግ እና ሀገር ውስጥ በተለያዩ ጉዳዮች ቅድሚያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

መሰል የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለባለድርሻ አካላት መሰጠቱ በጣም መሠረታዊና አዳዲስ የሆኑ የአሠራር ስርዓቶች የሚቀሰምበት መሆኑን የጠቀሱት ሃለፊው፣ በዚህም ለሕግ አስከባሪ አካላት ወቅቱን የዋጀ እና ተከታታይነት ያለው ሥልጠና እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

የሥልጠና መድረኩ በዛሬ ውሎው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ሰዎችን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ያሉ ዓለም ዓቀፍና ሀገር አቀፍ ህጎች ፣ቅድመ ምርመራ በተመለከተ፣ የሀብት ማስመለስ ጉዳዮችን አስመልክቶ፣ ከህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀሎች አንፃር የሚከናወነውን የቅድመ ጥቆማ ምርመራ እንዲሁም ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ በፍትሕ ሚኒስቴር የስራ ክፍል ሃላፊዎች እንዲሁም በአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ባለሙያዎች አማካኝነት ተዳሷል፡፡

ሥልጠናውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፍትሕ ሚኒስቴር እና የአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡

Tagged Under: adama • Amhara • anti-trafficking • Asset Recovery • border • border crossing • building • capacity • Capacity Building • crossing • enforcement • harari • human • Human Rights Violations • Human Trafficking • illegal • illegal immigration • Illegal Migration • international organization for migration (iom) • law • law enforcement training • Migration • ministry • ministry of justice (ethiopia) • oromia • Smuggling • trafficking • Training • Transnational crime
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

ተመሳሳይ ዜናዎች