ኢትዮጵያ በ116ኛው የዓለም የፍልሰት ድርጅት ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ወንጀልን ለመከላከልና መደበኛ ፍልሰትን ለማጠናከር ያላትን ቁርጠኝነት አስታወቀች

Ethiopia Reaffirms its Commitment to Safe and Development-Oriented Migration at the 116th IOM Council

ኢትዮጵያ በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም መደበኛና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማጠናከር በትኩረት እየሰራች መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርምያስ የማነብርሃን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው የተመድ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (International Organization on Migration) 116ኛ ምክር ቤት የሚኒስትሮች ስብሰባ ኢትዮጵያን በመወከል ተሳትፈዋል፡፡

እኤአ ከዲሴምበር 5-9/2025 በሚኒስትሮች ደረጃ በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፤ ኢትዮጵያ የፍልሰተኞች መነሻ፣ መተላለፊያና መዳረሻ አገር እንደመሆኗ መጠን ለፍልሰት ጉዳይ ዓይነተኛ ትኩረት በመስጠት እየሰራች ትገኛለች፡፡

በዚሁ መሰረት አገራችን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እንዲሁም መደበኛ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማጠናከር እና አስገዳጅ ፍልሰት የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመከላከል መሰረተ ሰፊ የፖሊሲ፣ የሕግ እና የተቋማዊ ማዕቀፎችን በማጠናከር ላይ እንደምትገኝ ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴዔታው እንደገለጹት ኢትዮጵያ ፍልሰት ችግር ሳይሆን በአግባቡና በቅንጅት ሊመራ የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ በክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሔራዊ ምክር ቤት እንዲሁም በፍትህ ሚኒስቴር የሚመራ ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ተቋቁሞ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አገራችን ፍልሰትን በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ በማካተት እንዲሁም ረቂቅ የፍልሰት ፖሊሲ በማዘጋጀትም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ አስረድተዋል፡፡

በሰው የመነገድና ሰውን በሕገ ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በተለይም ለፍልሰት ገፊ ምክንያቶችን በመለየትና ምላሽ በመስጠት እንዲሁም በሕግ ማስከበር፣ በድንበር ቁጥጥር፣ በመደበኛ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና የፍልሰትን መልካም ጎኖች ለልማት በማዋል ረገድ እንደ አገር እየተከናወኑ የሚገኙ ስትራቴጂክ ጉዳዮችንም በመድረኩ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በሁሉም ጉዳዮች አገራዊ ተግዳሮቶች የሆኑና የዓለም አቀፍ አጋሮችንና የመተላለፊያና የመዳረሻ አገራትን ድጋፍና ትብብር የሚጠይቁ ጉዳዮችንም በተመለከተ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ለካውንስሉ አቅርበዋል፡፡

የተመድ የፍልሰት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ማዳም ኤሚ ፖፕ በተገኙበት በተካሄደው በዚሁ የድርጅቱ 116ኛው የካውንስል ስብሰባ ከአፍሪካ አገሮች የሚመለከታቸው ሚኒስትሮች የተሳተፉበት መድረክ ተሳትፈዋል፡፡ መድረኩም በአህጉሪቱ የፍልሰት ጉዳዮች በተለይም መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን በመከላከል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን በማጠናከር፣ ተጋላጮችንና ተመላሾችን በዘላቂነት መልሶ በማቋቋምና በፍልሰትና ልማት ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዓለም የፍልሰት ስምምነት አተገባበር ጋር በተያያዘም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

Tagged Under: african charter on the rights and welfare of the child and healthcare administration and control authority Capital constitution of the federal democratic republic of ethiopia Convention on the Rights of the Child convention on the rights of the child (crc) council development Development Bank of Ethiopia development organization finance firm firms international international organization for migration international organization for migration (iom) Investment iom iom (international organization for migration) Migration National National Migration Council national science and technology research council organ organization ratio rea safe un
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች