ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር መካከለኛ አመራሮች እና ፈፃሚዎች በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Capacity Building Training on Project Management Being Provided to Mid-Level Leaders and Implementers of the FDRE Ministry of Justice

ሥልጠናውን በንግግር የከፈቱት በፍትሕ ሚኒስቴር የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ እና ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኖህ ታከለ ተቋሙ የ10 እና የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅዶችን በማዘጋጀት ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በስትራቴጂክ እቅዶቹ ውስጥ በርካታ ፕሮጀክቶች የሚገኙ በመሆኑ እነዚህን ፕጀክቶች ውጤታማ ለማድረግ ይህ ሥልጠና አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አቶ ኖህ ሥልጠናው 2ኛ ዙር መሆኑን በማስታወስ መካከለኛ አመራሩና ፈፃሚው በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ እንዲጎለበትና በፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያ ሥራዉ ከዕቅድ ጀምሮ የሚፈለገዉን ዉጤት እስከ ማስመዝገብ ድረስ ያለዉን ሂደት ከፕሮጀክት አስተዳደር መርህ አንጻር መቃኘት እንዲቻል ሥልጠናው ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡

የሥልጠናውም ዓላማ በፕሮጀክት አስተዳደር ዙሪያ የመካከለኛ አመራሩንና የፈጻሚውን የእውቀት ክህሎት ማዳበር እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ ሥልጠናውን የፍትሕ ሚኒስቴር እና ፕሪሳይስ (PRESISE) በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን ዛሬን ጨምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል፡፡

Tagged Under: building • capacity • Capacity Building • democratic • director • Education • FDRE • federal • federal democratic republic of ethiopia (fdre) • Justice • Justice System Reform • justice system strengthening • learning • management • mid-level managers • program management • project • project implementation • Project Management • reform • republic • skill development • Strategic Planning • system • Training
የቅርብ ጊዜ ዜናዎች