ከባድ ድርቅ እና ወይም በረሃማነት የሚያጠቃቸው አገሮች በተለይም በአፍሪካ ውስጥ በረሃማነትን የመከላከል ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽንን እ·ኤ·አ ኦክቶበር 15 ቀን 1994 ዓ.ም በፓሪስ ከተማ በኢትዮጵያም የተፈረመ ስለሆነ፤
ኮንቬንሽኑ በሥራ ላይ የሚውለው ከሃምሣ ሀገሮች የማጽደቂያ ሰነዶች ቀርበው ከተመዘገቡበት ጊዜ ከዘጠናኛው ቀን ጀምሮ እንደሚ ሆን በኮንቬንሽኑ ውስጥ የተመለከተ ስለሆነ፤
ይህንኑ ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 17 ቀን 1989 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል።
•
•