በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እና በኢጣልያ ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ዋስትና ለመስጠት ታህሣሥ 14 ቀን 1997 ዓም አዲስ አበባ ላይ ስምምነት የተፈረመ ስለሆነ፤
ስምምነቱ ሥራ ላይ የሚውለው የማጽደቂያ ሰነዶች ልውውጥ ከተደረገበት ዕለት አንድ ወር በኋላ እንደሚሆን በስም ምነቱ ውስጥ ስለተመለከተ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 30 ቀን 1989 ዓም ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል።