ለአርባረከቲ-ገለምሶ ሚቸታ የመንገድ ሥራ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መጠኑ 45 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል (አርባ አምስት ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል) የሚያስገኘው የብድር ስምምነት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በሳውዲ የልማት ፈንድ መካከል እ.አ.አ ኖቬምበር 20 ቀን 2013 በኩዌት የተፈረመ በመሆኑ፤
ይህንኑ የብድር ስምምነት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 20 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ (1) እና (12) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•