በማህበረሰቡ ዘንድ ሥር ሰዶ የቆየው ስለአካል ጉዳተኝነት ያለው የተሳሳተ ግንዛቤ በአካል ጉዳተኞች የሥራ ሥምሪት መብት ላይ የራሱን አሉታዊ ተጽእኖ ያሳደረ መሆኑን በመረደት፤
በሥራ ላይ የቆየው የአካል ጉዳተኞች የሥራ ስምሪት መብት አዋጅ ለአካል ጉዳተኞች የተወሰኑ የሥራ መደቦች እንዲለዩ መደንገጉ አካል ጉዳተኞች በችሎታቸው ተወዳድረው መሥራት የማይችሉ አድርጎ የሚቆጥር፣ ምቹ የሥራ ሁኔታ የማይፈጥርእና ተገቢውን የሕግ ከለላ የማይሰጥ ሆኖ በመገኘቱ፤
አገሪቱ ከምትከተለው እኩል የሥራ ዕድል መርሆ ጋር የሚጣጣም፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሥራ ሁኔታ የሚፈጥርና በሥራ ሥምሪት የሚደርስባቸውን መድልዎ በፍርድ መድረኮች በቀላሉ ለማስረዳት የሚያስችል አሠራር የሚዘረጋ አዲስ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 55 (1) እና (3) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
•
•
•
•
•